የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳዳር ይበልጣል አእምሮ ከካርቱም ስቴት ገዥ አይማን ካሊድ መሀመድ ካልድ ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

November 18, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካርቱም የኢፌዴሪ ልዩ መልዕከተኛና ባለመሉ ስልጣን አምባሳዳር ይበልጣል አእምሮ ከካርቱም ስቴት ገዥ አይማን ካሊድ መሀመድ ካልድ ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደሩ ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይና ህግ ማስከበር ስራ ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሱዳን ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ክለብ የሚያገለግል ተጨማሪ ቦታ እንዲሰጥ ለአስተዳዳሪው ጥያቄ ማቅረባቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኢምባሲ አሳውቋል፡፡