Fana: At a Speed of Life!

የህወሃት ጁንታ ለህግ እስከሚቀርብ ድረስ ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል- የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የህወሃት ጁንታ ለህግ እስከሚቀርብ ድረስ ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ።

ከፍተኛ አመራሮቹ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል የደም ልገሳ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

የክልሉ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ጁል ናንጋል ÷ ሀገርን ለማዳን ከፍተኛ መስዕዋትነት እየከፈለ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር ለመግለጽ ደም መለገሳቸውን ገልፀዋል።

የህወሃት ጽንፈኛው ቡድን አሰልጥኖ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ባሰማራቸው የጥፋት ቡድኖች እየተፈፀመ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ማስቆጣቱን ጠቅሰው ÷ጁንታው ለህግ እስኪቀርብ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አቶ ኡቦንግ ኡቶውና አቶ ጋትሉዋክ ጋች በበኩላቸው÷ ጽንፈኛው ህወሃት የፈፀመውን አስነዋሪ ተግባር ተከትሎ ግዳጅ ላይ ለሚገኘው ከሀገር አልፎ ለቀጠናዊ ሰላም ሚናው ከፍተኛ ለሆነው መከላከያ ሰራዊት ከጎኑ መሆናቸውን ለማሳየት ደም መለገሳቸውን ገልፀዋል።

ከደም ልገሳው ጎን ለጎን ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ የማቴሪያልና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ነው የተናገሩት።

አያይዘውም ሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ከሀገር መነከላከለያ ጎን ሊሆን ይገባል ማለታቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.