Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ፀረ-ተህዋሲያን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ፀረ-ተህዋሲያን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት “ፀረ-ተህዋሲያንን-በጥንቃቄ ይጠቀሙ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ÷በፀረ-ተህዋሲያን እና በሌሎች ፀረ ጀርም መድኃኒቶች ላይ እያደገ የመጣውን የመላመድ ችግር ለመቅረፍ ውጤታማ የፀረ-ተህዋሲያን የአጠቃቀም ግንዛቤን የማጎልበት ትምህርት እና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የጸረ ተሕዋስያን መድኃኒቶችን በሐኪም ትዕዛዝ ብቻና በታዘዘው መሰረት መውሰድ ተገቢ መሆኑንም ነው የገለጹት።

 

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.