በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ከሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ከሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
ውይይቱ በአዲስ አበባ ኢሊሌ ሆቴል ነው የተካሄደው፡፡
በውይይቱ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ የህወሓት ጁንታ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል፡፡
እንዲሁም የፌደራል መንግስት በህወሓት ጁንታ ላይ እየወሰደ ለሚገኘው ህግ የማስከበር ዘመቻ ያላቸውን ድጋፍም ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በትግራይ ክልል ያለው ሰብዓዊ እርዳታ እና ድጋፍ እንደሚያሳስባቸውም ነው የገለጹት፡፡
መንግስት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎችም የሰብዓዊ እርዳታ እና ድጋፍ እንዲሰጥ እና ሁኔታዎችን እንዲያመቻችም ጠይቀዋል፡፡
በሰላማዊት ካሳ