ም/ጠ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሼኬዲ ጋር ተወያዩ።
አቶ ደመቀ በነበራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ ባለፉት ሁለት ቀናት በኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ባደረጉት ጉብኝት ከሀገራቱ መሪዎች ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።
በቆይታቸውም የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ የሚገኘውን ህግ የማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡