Fana: At a Speed of Life!

ለሰራዊቱ እየተሰጠ ያለው ድጋፍና ክብር ዘመቻውን በፍጥነት ለመቋጨት ጉልበት ነው – የአየር ኃይል ምስራቅ ምድብ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍቢሲ) መላው ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እየሰጠ ያለው ድጋፍና ክብር የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ በፍጥነትና በስኬት እንዲጠናቀቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የኢፌዴሪ አየር ኃይል የምስራቅ ምድብ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አበበ ለገሰ አስታወቁ፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር የጀልዴሳ ገጠር ክላስተር ነዋሪ አርብቶ አደሮች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 430 ሺህ ብር የሚያወጡ ስምንት ግመሎችና አንድ ሰንጋ አበርክተዋል፡፡

ኮሎኔል አበበ በዚህ ወቅት ህዝቡ የሰራዊቱን የህግ ማስከበር ዘመቻ በሞራል፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በሙያ፣ በደም ልገሳና በሌሎችም ድጋፎች አጋርነቱን እያሳየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህ ደግሞ ህግ የማስከበር ዘመቻው በአጭር ጊዜ በስኬት እንዲጠናቀቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፤ ህዝቡ ላሳየው ክብርና ድጋፍ በሰራዊቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል አዛዥ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ዘውዴ በበኩላቸው መላው የሀገሪቱ ዜጎች ለሠራዊቱ ያሳዩት ክብርና እየለገሱ ያለው ድጋፍ ሠራዊቱ ሀገራዊ ተልዕኮውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዘው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.