Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሚኒስቴር ከተለያዩ ሀገራት ለተወከሉ ወታደራዊ አታሼዎች ማብራሪያ እየሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ህዳር 10 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከተለያዩ ሀገራት ለተወከሉ የወታደራዊ አታሼዎች በህልውና ዘመቻው ዙሪያ ማብራሪያ እየሰጠ ነው።

የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀንአ ያደታ በተገኙበት ነው ከ45 ሀገራት ለመጡ የወታደራዊ አታሼዋች ማብራሪያው እየተሰጠ የሚገኘው።

ፅንፈኛ ቡድኑ ላይ እየተወሰደ ያለው የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ ግብ፣ መነሻና አሁን ያለበት ደረጃን አስመልክቶ ነው ገለፃው ትኩረት ያደረገው።

ሚኒስትሩ ሁሉንም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲፈፅም እንደነበር ያነሱት የሀገር መከላከያን በመውጋት ክህደት የፈፀመውን ቡድን ለፍርድ ማቅረብ አስፈላጊና ግዴታ በመሆኑ የተገባበት ዘመቻ ስለመሆኑ አስረድተዋል።

ቡድኑ ራሱን ለጦርነት ሲያዘጋጅ መቆየቱ ሳያንስ ህገመንግስቱን የተፃረሩ በርካታ ተግባራትን መፈፀሙን እና ለሀገር ህልውና ስጋት የሆነውን ቡድን ወደ ህግ ማቅረብ የዘመቻው ግብ እንደሆነም ተብራርቶላቸዋል።

ቡድኑ በሚነዛው ፕሮፓጋንዳ ዘመቻው በህዝቡ ላይ እየተወሰደ ያለ እርምጃ በማስመሰል ለማቅረብ እና አለማአቀፋዊ መልክ ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑ እና ይህም ተኩስ አቁም ሰበብ ጊዜ ለመግዛት ጥረት እያደረገ መሆኑም ተገልፆላቸዋል።

ዘመቻውም ህዝቡን እና ንፁሃንን ከወንጀለኛው ቡድን በለየ አኳኋን እየተካሄደ መሆኑንም ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

 

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.