Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና የከተማዋ ነዋሪዎች ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 10 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና የከተማዋ ነዋሪዎች 11ነጥብ 19 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል ።
ከገንዘብ ድጋፉ ባለፈም የከተማዋ አስተዳደርና ነዋሪዎቹ 41 ሰንጋ በሬዎችን ለሰራዊቱ አበርክተዋል።
ለሰራዊቱ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ፣ባላሃብቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በብር እና በአይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን የከተማው አስተዳደር አስታውቋል ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ÷ የከተማውን ሰላም በመጠበቅ እና ለሰላም ዘብ በመቆም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ከንቲባው አያይዘውም ለሀገር መከታ ለሆነው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.