Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ያደረጉትን ድጋፍ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪዎች ከ900 በላይ የእርድ ከብቶችንና ከ700 ኩንታል በላይ የምግብ እህል ለኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የዞኑ ነዋሪዎች በአጠቃላይ 520 ሰንጋዎች፣ 350 በጎች፣ 60 ፍየሎች፣ 520 ኩንታል ስንዴ፣ 110 ኩንታል በቆሎ እና 100 ኩንታል ቡና በድጋፍ አሰባስበዋል፡፡
ድጋፉንም ዛሬ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ከዞኑ አመራር ተረክበዋል፡፡
አቶ ፍቃዱ ድጋፉን ከዞኑ አመራር ሲረከቡ ለተደረገው ትብብር ሁሉ አመስግነዋል፡፡
ሃላፊው የህወሓት ጁንታ ቡድን የሀገር ኩራትና መከታ በሆነው የሰሜን እዝ ላይ የሽብር ጥቃት መፈፀሙን አንስተው፥ ድጋፉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ዘመቻ ታላቅ አቅም መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አበራ ቡኖ በበኩላቸው ዞኑ ከነበረበት የፀጥታ ችግር ወጥቶ ወደ ልማት ስራዎችን መዞሩን እና ለሀገር ደህንነትና ሰላምም የድርሻውን እያበረከተ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.