የኦሮሚያ አራት ዞኖች ለመከላከያ ሰራዊት 705 ሰንጋዎችና 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቦረና ዞን፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን እና ፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ 705 ሰንጋዎችና 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
ከአራቱ ዞኖች የተወከሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና አባገዳዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች በኢፌዴሪ ምድር ሀይል ተገኝተው የነዋሪዎችን ስጦታ አስረክበዋል።
ተወካዮቹ ወደፊትም መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በዚሁ የድጋፍ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ ከዞኖቹ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።