Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ሁለተኛው ክስ እንዲሻሻል ፍርድ ቤቱ አዘዘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ሁለተኛው ክስ እንዲሻሻል ፍርድቤቱ አዘዘ፡፡
አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ሁለተኛው ህገመንግስቱን ለማፍረስ በማሰብ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት ወንጀል የቀረበባቸው ክስ ነው እንዲሻሻል የታዘዘው።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ወንጀል ችሎት በባለፈው ቀጠሮው ክሱ ላይ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠትና አቶ ልደቱ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ተለዋጭ ሰጥቶ ነበር፡፡
በዚህ ቀጠሮ መሰረት ፍርድ ቤቱ ዛሬ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ አንቀጽና ዝርዝሩ አይጣጣምም ሲል ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ አዟል።
አቶ ልደቱ የጠየቁት ዋስትና ጥያቄን ክሱ ተሻሻሎ ሲመጣ ለመመልከትና ብይን ለመስጠት ለህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በታሪክ አዱኛ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.