የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ደረጀ ድጉማ ለቲቢ በሽታ እየተሰጠ ባለው ምላሽ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ

By Abrham Fekede

November 20, 2020

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በአፍሪካ ለቲቢ በሽታ እየተሰጠ ባለው ምላሽ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ የተለያዩ ሃገራት የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል፡፡

በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ውይይት ላይ ለቲቢ በሽታ በአፍሪካ እየተሰጠ ባለው ምላሽ ዙሪያ መምከራቸውን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

ውይይቱን ግሎባል ፈንድ የተባለው ተቋም ነው ያዘጋጀው፡፡ ውይይቱ “ይህንን ያልተለመደ ወቅት ባልተለመደ አዲስ ሐሳብ” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው፡፡