Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት 452 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 5 ሺህ 488 የላብራቶሪ ምርመራ 452ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 104 ሺህ 879 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈ የ13 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 620 መድረሱንም አመላክተዋል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 342 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 65 ሺህ 325 መድረሱም ተገልጿል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 585 ሺህ 559 ሰዎች ምርመራ ተደርጓል፡፡
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 37 ሺህ 932ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 315 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.