Fana: At a Speed of Life!

ኤምባሲው ለቀድሞው የባህር ኃይል አባላት ጥሪ እንዳቀረበ ተደርጎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በለንደን የኢፌዴሪ ኤምባሲ ለቀድሞው የባህር ኃይል አባላት ጥሪ ያለማቅረቡን አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው እንደገለፀው በዩናይትድ ኪንግደም በሰሜን አየርላንድ ለሚኖሩ ለቀድሞው መከላከያ የባህር ኃይል መኮንኖች የጥሪ ደብዳቤ እንደፃፈ ተደርጎ በየማህበራዊ ሚዲያው እየተዘዋወረ ያለው ሰነድ የሱ ያለመሆኑን አሳውቋል፡፡

ሰነዱ በጥብቅ ምስጢር እንደተፃፈ በሚገልፅ የተሰራጨው ዘገባ ሀሰተኛ ነውም ብሏል፡፡

በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማንኛውም መረጃ ፈላጊ ያለገደብ በግልፅ መረጃ ማግኘት እንደሚችልና ያላስፈላጊ ውዥንብር ውስጥ እንዳይገባ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የተሰራጨው ዘገባ ሆን ተብሎ በህወሓት የጥፋ ቡድን አክቲቪስቶች የተፈፀመ መሆኑንም አመላክቷል፡፡

ደብዳቤውም የፈጠራና ሀሰተኛ መሆንን አሳውቋል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.