Fana: At a Speed of Life!

ማይክ ፖምፔዮ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2013()ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት ሊያደርጉ ነው፡፡

ጉብኝቱ በዋናነት ዋሽንግተን ለሃገሪቱ በምትሸጠው የጦር መሳሪያ ላይ ያተኩራል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ባለፈም የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶችን ጨምሮ የባህረ ሰላጤው ሃገራት ከእስራኤል ጋር ግንኙነታቸውን መደበኛ ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ያለመ መሆኑንም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከአቡዳቢው ልዑል ጋር ይመክራሉም ነው የተባለው ፡፡

ከዚህ ባለፈም በጉዳዮቹ ላይ ውይይት ለማድረግ ከመሃመድን ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር እንደሚገናኙም ተገልጿል፡፡

ማይክ ፖምፔዮ እስካሁን ድረስ ወደ ፈረንሳይ፣ ቱርክ፣ ጆርጂያ እና እስራኤል በማቅናት ጉብኝት ሲያደርጉ የሃገራቱ መሪዎች አዲስ ለተመረጡት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.