Fana: At a Speed of Life!

ጁንታው ያደራጃቸው የጥፋት ሃይሎች እየተደመሰሱ ነው – በምዕራብ ዕዝ የ22ኛ ክፍል ጦር ዋና አዛዥ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማደናቀፍ ጁንታው ህወሃት አደራጅቶ የላካቸው የጥፋት ሃይሎች እየተደመሰሱ መሆኑን በሀገር መከላከያ ምዕራብ ዕዝ የ22ኛ ክፍል ጦር ዋና አዛዥ አስታወቁ፡፡
የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ነገሪ ቶሊና ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያን መበታተን ዋነኛ ግቡ ያደረገው የህወሃት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት እጅግ የሚያም እና የክፍለ ጦሩን ሠራዊት አባላት ያስቆጣ ነው፡፡
“አባቶቻችን ጀግንነት እና አንድነትን ነው ያስተማሩን” ያሉት አዛዡ÷ የ22ኛ ክፍለ ጦር የህዳሴው ግድብ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አካባቢውን በመጠበቅ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ጁንታው ያደራጃቸው “ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው” በሚል ፕሮፓጋንዳ የተመሩ ኦነግ ሸኔ እና ሌሎችም የህወሃት የጥፋት ቡድኖች ከውጪ ሃይል ጋር በመቀናጀት ከምዕራብ ወለጋ እስከ መተከል የሚያደርጉት የጥፋት ሴራ እንዳለ አዛዡ ጠቁመዋል፡፡
የአካባቢው ህብረተሰብ ከመቼውም በላይ ከሠራዊቱ ጎን መሆኑን የገለጹት ብርጋዴር ጀኔራል ነገሪ÷ በመተከል ዞን የህዳሴ ግድብ አካባቢ የጥፋት ቅጥረኞቹ ልክ እንደጁንታው እየተደመሰሱ መሆኑን አስታወቀዋል፡፡
በጁንታው ተላላኪዎች ላይ እየተወሰደ የሚገኘው እርምጃ ከሌሎች የጸጥታ አስከባሪዎች ጋር በመተባበር እንደሆነም አስረድተዋል ኢል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.