የሀገር ውስጥ ዜና

መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸው 19 ሐኪሞች አስመረቀ

By Tibebu Kebede

November 21, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ዶክትሬት የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸው 19 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ 99 የህክምና ዶክተሮችን አሰልጥኖ አስመርቋል።

በዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጄይላን ቃሲም ሆስፒታሉ ለአካባቢው ማህበረሰብ ከሚሰጠው የህክምና አገልግሎት በተጓዳኝ በተለያዩ የህክምና ሙያዎች ስልጠና እየሰጠ እንዳለ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በ1999 ዓ.ም 742 ተማሪዎች ተቀብሎ ስራ የጀመረው መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አሁን ላይ ከ24 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች አሉት።