Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ቡድን የሰራዊቱን ሕግ የማስከበር እርምጃ መቋቋም እንደተሳነው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጁንታው የህወሐት ቡድን የሰራዊቱን ሕግ የማስከበር እርምጃ መቋቋም እንደተሳነው የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ገለጹ።

ጄኔራል መኮንኑ የሠራዊቱን ፈጣን የማጥቃት እንቅሰቃሴን አስመልክተው ገለፃ አድርገዋል።

ፅንፈኛው የህወሃት ቡድን የሠራዊታቱን ወቅታዊ አቋም በተሳሳተ መንገድ ገምግሞ በድሮ የጫካ ስሌት ወደ ውጊያ በመግባቱ ለውርደት ተዳርጓል ብለዋል።

ብ/ጄ ተስፋዬ አክለውም ፅንፈኛው ቡድን ልዩ ኃይል ብሎ የሚጠራውን ታጣቂና ሚሊሻውን ከፊት አሰልፎ ፣ ከሰራዊቱ በተለያየ ምክንያት የወጡ ከሃዲያንን ከኋላ በማሰለፍ በግዴታ እንዲዋጉ እያደረገ ነው ብለዋል።

ፅንፈኛው የህወሃት ጁንታ ህዝቡን ከመናቁ የነተነሳ ፣ የልማት አውታሮችን እያወደመ እንደሚገኝ ተናግረው ፣ ይህም የሽንፈቱ ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።

ጁንታው ከአሁን በኋላ ያለው ብቸኛው አማራጭ ተዋግቶ መሞት አሊያም እጅ መስጠት ብቻ ነው ማለታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.