በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሠፈራ ጣቢያ ለጥፋት አላማ ሊውል የነበረ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሠፈራ ጣቢያ ለጥፋት አላማ ሊውል የነበረ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን በሰሜን እዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ጄኔራል ሙሉአለም አድማሱ አስታወቁ።
በቁጥጥር ስር የዋሉ የጦር መሳሪያዎችም 207 ክላሽ፣ 9 ሺህ 80 ጥይት፣ 26 አርባ ጎራሽ ፣ 18 አስር ጎራሽ ፣ የተለያዩ ሽጉጦች እና ማካሮፍ 26፣ ስታር 5፣ fort five 4፣ Breta 1፣ 2 ካርታ እንዲሁም 108 የተለያዩ የቦምብ አይነቶች ናቸው ።
ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች እንዲሠፍሩ ሲደረግበት በቆየው የመኖሪያ ጣቢያ በተደረገ ኦፕሬሽን ያለምንም የተኩስ ልውውጥ በልዩ ወታደራዊ ጥበብ መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጄነራሉ ገልፀዋል።