Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚኒሶታና ሎስ አንጀለስ የቆንስላ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚኒሶታና ሎስ አንጀለስ የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ጋር በመሆን በአሜሪካ በሁሉም ግዛቶች ከሚገኙ ከ500 ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ውይይት በሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣታት ውይይታቸውን ማጠናቀቃቸውን በዋሽንግተን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
በዚህም ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን በሰሜን እዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጫፍ የረገጠ ሃክህደት ጥቃት እና በማይካድራ እና በሌሎች አካባቢዎች በግፍ የተፈጸሙ ጥቃቶችን አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል።
መንግስት ተገዶ የገባበትን የህግ ማስከበር ዘመቻ በአሸናፊነት ለመወጣት የሚያደርግውን ጥረት እንደሚደግፉም አስታውቀዋል።
ለመከላከያ ሰራዊት የሞራል እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን እንደሚገልፁም ተናግረዋል፡፡
የጁንታውን ቡድን ተላላኪዎቹ የሀሰት ወሬ ዘመቻ ለማጋለጥ እና ትክክለኛውን የቡድኑን ማንነት ለዓለም ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ፣ ለወዳጅ ሀገራት መንግስታት እና ለውሳኔ ሰጪ አካላት ለማሳወቅም በተደራጀ መንገድ ለመስራት ወስነዋል።
ቡድኑ በሀገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ስም የሚያካሂደውን የፖለቲካ ንግድ በማውገዝ፣ የትግራይ ህዝብ ከመላው ኢትዮጵያውያን ወንድም እና እህት ጋር ሆኖ ይህን ቡድን እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ እና የህግ አስፈፃሚ አካላት፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እና ሌሎች መንግስትታ ሁኔታውን በሚገባ አውቀው ቡድኑን ወደ ህግ በማቅረብ ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ እንደዜጋ የተቀናጀ እና የተናበበ ሰራ እንሰራለንም ነው ያሉት፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.