Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከተዋናይትና እና በበጎ አድራጎት ስራ ከምትታወቀው አንጀሊና ጆሊ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በልማት፣ በሴቶች እና በስደተኞች ጉዳይ ዙሪያ መምከራቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ የአንጀሊና  ጉብኝት ኢትዮጵያ የሴቶችን ጉዳይ ጨምሮ በሁሉም መስኮች አዲስ ምዕራፍ እየተከፈተ ባለበት እና በአስገራሚ የለውጥ ጎዳና ላይ ባለችበት ወቅት የተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

ይህም ስለ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ያለውን አተያይና አስተሳሰብ ለመለወጥ የማይናቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን አውስተዋል።

ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ በበኩሏ ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የመጣችው በህጻናትና ሴቶች እንዲሁም ጤና ላይ መስራት የሚቻልባቸውን እድሎች ለማየት መሆኑን ገልፃለች።

አንጀሊና ጆሊ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ባሳለፍነው እሁድ ዕለት ከልጆቿ ጋር ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥም የ14 አመቷ ዘሃራ በትውልድ ኢትዮጵያዊት ነች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.