Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት 418 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 963 የላብራቶሪ ምርመራ 418 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 106 ሺህ 203 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈ የ4 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 651 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 148 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 65 ሺህ 839 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 600 ሺህ 606 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 106 ሺህ 203 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 38 ሺህ 711 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 326 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.