Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሞላ መልካሙ የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 8ኛ ዓመት 2ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በጉባኤው አቶ ሞላ መልካሙን የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል፡፡

በዛሬው ጉባኤ ሌሎች ልዩ ልዩ ሹመቶችን ያፀድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አቶ ሞላ መልካሙ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አዲሱ ከንቲባ የትምህርት ዝግጅት በ1993 ዓ.ም በጎንደር መምህራን ኮሌጅ በሒሳብ ትምህርት ዲፕሎማቸውን አግኝተዋል ።

በ2ዐዐዐ ዓ.ም ደግሞ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በdisaster risk management and sustainable Development ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ማግኘታቸው ነው የተነገረው።

ከዚህ ባለፈም በ2ዐዐ9 ዓ.ም ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ Executive master of Business administration ትምህርት 2ኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

በስራ ዘርፍም ከ1993 እስከ 2ዐዐዐ ዓ.ም በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች በተለያየ የአመራር ቦታ ላይ ተመድበው አገልግለዋል፡፡

ከ2ዐዐ1 እስከ 2ዐ11 ዓ.ም ደግሞ በቀድሞው ሰሜን ጎንደር በአሁኑ ምዕራብ ጎንደር እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች፥ የዞን ዋና አስተዳዳሪነትን ጨምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ተመድበው በታማኝነት የስራ ተነሳሽነትና ውጤታማነት አገልግለዋል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.