Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጃዋር መሃመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሃምዛ አዳነን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች የንብረት እግድ ይነሳልን ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ጃዋር መሃመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሃምዛ አዳነ ወይም ሃምዛ ቦረናን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ዐቃቤ ህግ ያገደባቸውን የንብረት እግድ ይነሳልን ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ሆነ፡፡ 

የንብረቱን እግድ በተለመለከተ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸውን ተመልክቷል፡፡

አቶ ጁዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሃምዛ አዳነ ወይም ሃምዛ ቦረና በችሎቱ ያልተገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ ተከሳሾች ግን ተገኝተዋል፡፡

ለምን እንዳልተገኙ ለችሎቱ ያስረዱት የተከሳሽ ጠበቃ ለሃገሪቱ ደህንነት ሲባል አንቀርብም ማለታቸውን አብራርተዋል፡፡

ይሁንና ፍርድ ቤቱ የተከሳሾች የታገደው ንብረታችን ይነሳልን አቤቱታን እና ዐቃቤ ህግ የንብረታቸው የወንጀል ፍሬ ነው መነሳት የለበትም ሲል ያቀረበውን ምላሽ መርምሮ ችሎቱ የታገደውን ንብረት ሊነሳ አይገባም ሲል ብይን ሰጥቷል፡፡

ነገር ግን የተከሳሾችን ቤተሰብ ቀለብ በተለመለከተ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ለህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ አጠቃላይ ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ላይ የሚያቀርቡት የክስ መቃወሚያ በመመልከት አንደኛ የህገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ለህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

 

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.