የሀገር ውስጥ ዜና

የቁም እንስሳት ነጋዴዎች ማህበር ከ4 ሚሊየን በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

November 24, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ባቀረቡት የድጋፍ ጥሪ መሰረት የቁም እንስሳት ነጋዴዎች ማህበር ከ4 ሚሊየን በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡

ማህበሩ 160 ሰንጋዎችን ጨምሮ 2 ሺህ ሊትር ዘይት ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡

ይህም በገንዘም ሲሰላ ከ4 ሚሊየን በላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ድጋፉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ተረክበዋል፡፡

ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንዳሉት÷ መንግስት የጀመረው ህግን የማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ህብረተሰቡም የቻለውን እንዲያደርግ እና እያደረገ ያለው ድጋፍ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ