Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ 25 የሂዝቦላህ አባላትን መግደሏን ተከትሎ ኢራቅ እርምጃውን አውግዛለች

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢራቅ አሜሪካ በኢራን ድጋፍ በሚደረግለት የካታይብ ሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ላይ የፈጸመችውን ጥቃት  አውግዛለች።

የአሜሪካ  ባሳለፍነው እሁድ ዕለት በኢራን በሚደገፉ ታጣቂዎች ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 25 የቡድኑ አባላት ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

ጥቃቱ በኢራቅ የሚንቀሳቀሱ እና በኢራን መንግስት እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው ካታይብ ሂዝቦላህ የተሰኙ ታጣቂ ቡድን  በቅርቡ ባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ወታደራዊ ማዕከል ላይ ለፈጸሙት ጥቃት አጸፋ መሆኑ ተነግሯል።

ድርጊቱን ተከትሎም የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር አደል አበድል ማሃዲ አሜሪካን በጽኑ አውግዘዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የአሜሪካ ወታደሮች በታጣቂዎች ላይ የፈጸሙት ጥቃት የኢራቅን ሉዓላዊነት የሚጥስ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ጥቃቱ ሃላፊነት የጎደለው  እና ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑ ባሻገር በቀጠናው በርካታ ችግሮችን ሊያስከትል እና ውጤቱም የከፍ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

ስለሆነም ባግዳድ በአሁኑ ወቅት ከዋሽንግተን ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት በትኩረት ማጤን እና ማሻሻል ይገባታል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በሌላ በኩል የኢራቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጉዳዩ ዙሪያ በሀገሪቱ የአሜሪካ አምባሳደር ጋር የሚመክሩ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢራን ብሄራዊ ዘብ አብዮት በበከሉ  በቅርቡ አሜሪካ  በቀጠናው እያከናወነች ያለችውን ጥቃት ጸብ አጫሪ ድርጊት ሲሉ ኮንነዋል።

 

 

ምንጭ ፦ቢቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.