የሀገር ውስጥ ዜና

በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ለተፈናቀሉ ዜጎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል- ወይዘሮ ሙፈሪያት

By Tibebu Kebede

November 24, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ለተፈናቀሉ ዜጎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፊሪያት ካሚል አስታወቁ።

ዘርፈ ብዙ የአስቸኳይ ጊዜ ቅኝት ቡድን በሰበሰበው ወቅታዊ ሪፖርት ዙርያ አለም አቀፍ ለጋሾች ባሉበት በጋራ ወይይት መካሄዱ ተጠቁሟል።

ለተፈናቀሉ ወገኖች የእለት ደራሽ ድጋፍ በተቻለ ፍጥነት ከማድረስና ጎን ለጎን ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ተግባር መከናወን እንደሚኖርበት  በውይይቱ ላይ መሳቱን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል ፡፡

ከዚህ በፊት ባጋጠሙ የተለያዩ ተፈጥሯዊም ይሁን ሰው ሰራሽ አደጋዎች ላይ አስቸኳይ እርዳታ ያቀረቡ ተቋማት አሁንም ባጋጠመው ችግር ላይም ትብብራቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ገልፀዋል።

ሚኒስትሯ  ለተፈናቀሉ ዜጎች የመድረስ ስራ ከምንም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ነው ብለዋል፡፡