የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉጂ ዲ ማዮ ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

November 24, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉጂ ዲ ማዮ ጋር ተወያይተዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ የመንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ጣሊያን ሮም ይገኛል።

በሮም ቆይታቸውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉጂ ዲ ማዮ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በቆይታቸውም አጠቃላይ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና በሁለቱ ሃገራት ታሪካዊ  ግንኙነት እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ትስስር በሚያጠናክሩ ርዕሶች ዙሪያ በጋራ መክረዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ የመንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ከጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር  ጁሴፔ ኮንቴ ጋር መወያየታቸውም ይታወቃል።