Fana: At a Speed of Life!

በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደር የሚደረገው የገቢ ወጪ እንቅስቃሴ ላይ ምንም አይነት ተጽዕኖ እንዳይኖር መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደር የሚደረገው የገቢ ወጪ እንቅስቃሴ ላይ ምንም አይነት ተጽዕኖ እንዳይኖር መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ።

መንግስት ህግን ለማስከበርና የሃገሪቱን ደህንነት ለመጠበቅ በእኩዩ የህውሓት ጁንታ ላይ እያካሄደ ከሚገኘው ዘመቻ ጋር በተገናኘ 95 በመቶ የሚሆነው የሃገሪቱን የገቢና ወጪ እንቅስቃሴ የሚደረግበት የኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደር ላይ ምንም አይነት እክል እንዳይገጥመው ከጂቡቲ መንግስት ጋር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በቅርበት እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

በጂቡቲ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ÷ ኮሪደሩ ደህንነቱና ጸጥታው የተጠበቀ እንዲሆን ከሚመለከታቸው የጂቡቲ ኃላፊዎች ጋር ቅንጅታዊ ስራ መስራት መቻሉን ገልጸዋል።

በተለይም በየቀኑ ወደ ሃገር መግባት ያለባቸው እንደ ነዳጅ ያሉ ምርቶች ያለምንም ችግር ወደ መዳረሻቸው እንዲሄዱ ማድረግ ተችሏልም ነው ያሉት፡፡
አምባሳደሩ አያይዘውም በጂቡቲም ሆነ በታጆራ ወደቦች ውስጥ የሚደረጉ የዕለት ተዕለት የወደብ ክንውኖች እንደ ወትሮው የቀጠሉ በመሆኑ በመንግስት በኩል ገቢና ወጪ ምርቶችንና ሸቀጦችን ለማንቀሳቀስ በተያዘው እቅድ መሰረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጂቡቲ ከሚገኙ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች፣ የትራንስፖርት ማህበራት ተወካዮችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት መሰራቱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚነዙት አንዳንድ ውዥንብሮች ሳያደናግጣቸው ስራቸውን እንዲሰሩ ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.