Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በወቅታዊነት በሚከናወኑ ተግባራት የሚከሰቱ የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል የቅሬታ መቀበያ ስልክ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በወቅታዊነት በሚከናወኑ ተግባራት የሚከሰቱ የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል የቅሬታ መቀበያ ስልክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
በህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ላይ መንግስት የሚወስደውን ህግን የማስከበር እርምጃ ተከትሎ በአዲስ አበባ የጁንታው ቡድን ተላላኪዎች ሊያስከትሉ የሚችሉትን ጥፋት ለመከላከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ ባደረገው በጥናት ላይ የተመረኮዘ አሰሳና ፍተሻ በርካታ ውጤቶች እየተገኙ መጥተዋል፡፡
ሆኖም በስራ አፈፃፀም ላይ የታዩ ጉድለቶች እንዲስተካከሉ ከህብረተሰቡ የሚመጡ አስተያየቶችና ቅሬታዎች በመኖራቸው መረጃዎችን ለመቀበል ስልክ ማዘጋጀቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ ባስተላለፈው መልዕክትም የሚከሰቱ የሰብዓዊ ጥሰቶች እንዲሁም በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ተገቢ ያልሆነ ጫና በአጠቃላይ ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የተገናኙ ማንኛውም አይነት ቅሬታዎች አሉኝ የሚል ነዋሪ በስልክ ቁጥር በ011-8-69-45-02 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚችል ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.