የሀገር ውስጥ ዜና

የጊኒ ዎርምን ለማጥፋት በሚቻልበት አግባብ ላይ የሚመክር መድረክ እየተካሄደ ነው

By Abrham Fekede

November 25, 2020

አበባ፣ ህዳር 16፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በኢትዮጵያ የጊኒ ዎርምን ማጥፋት በሚቻልበት አግባብ ላይ የሚመክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

መርሃ ግብሩ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

በመድረኩ ጊኒ ዎርምን ለማጥፋት ዋና ዋና ተግዳሮቶች እንደሚለዩም ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ሁለገብ ትብብርን ይበልጥ በማጠናከር በሽታውን ጨርሶ ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የሚያስችሉ አዳዲስ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ላይ እንደሚያተኩሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡