Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች የተሳተፉበት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች የተሳተፉበት የ2013 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ መድረኩን ሲያስጀምሩ፤ ተቋማዊ አሰራርን ጠንካራ ለማድረግ ተግባርን መሰረት ተደርጎ የሚገነባ የአመራር ስርዓት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የክልሉን ህዝብ የልማት እና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚነትን ዓላማ ያደረገ መድረክ መሆኑንም አንስተዋል።

የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው ከክልል ምስረታ ወዲህ በየዘርፉ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ የተገኙ ውጤቶችና በስራ አፈጻፀም የታዩ ጉድለቶችን በመለየት የአመራር ስርዓትን ማጠናከርን ታሳቢ ያደረገ መድረክ እንደሆነ ገልፀዋል።

የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና በፖለቲካው ዘርፍ ጠንካራ እና ተፎካካሪ ክልል ለማድረግ በሚያስችል ደረጃ በመድረኩ ሰፊ ውይይት የሚደረግ ሲሆን መድረኩ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት እንደሚቆይ ከክልሉ መንግስት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመድረኩም ላይ የክልሉ ጠቅላላ አመራር፣ የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የፊት አመራሮች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.