Fana: At a Speed of Life!

በሰበታ ከተማ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከሸፈ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰበታ ከተማ 04 ቀበሌ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ ጉዳት ሳያደርስ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከሸፈ፡፡
ፈንጂው መሀመድ ረጃ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የተገኘ መሆኑን የሰበታ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
መስጂድ አቅራቢያ ላይ መጠመዱ በተቋሙና በምዕመናን ላይ ጉዳት ለማድረስ ታቅዶ የተፈፀመ መሆኑን የቀበሌው አስተዳደርና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ተሬሳ ገልፀዋል፡፡
ይሁንና በህብረተሰቡ ጥቆማ ጉዳት ሳያደርስ መክሸፉን ተናግረዋል፡፡
ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጥቆማ ሲደርሰው በፍጥነት ወደ አካባቢው በማምራት የማክሸፍ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
ህብረተሰቡ አካባቢውን ከጥፋት ኃይሎች በንቃት እንዲጠብቅና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲታዘብ ጥቆማ እንዲያደርሰው የከተማው ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.