Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ማስክ ሳምንት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) ሳምንት በኢትዮጵያ እንዲሁም በመላው አፍሪካ ከሕዳር 14 ቀን ጀምሮ እየተከበረ ነው፡፡

‘ማስክ አፍሪካ’ በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ንቅናቄ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብልን በአግባቡ ማድረግ የሚኖረውን ጠቀሜታ ለማስተማር እና በአግባቡ ለመጠቀም የሚያግዝ ሲሆን እስከ ሕዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የሚከበር ነው ተብሏል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጉዳቱ እየጨመረ እና በሕብረተሰብ ጤና እንዲሁም ማህበራዊ ሁነቶች ላይ ጫና በሚያሳድርበት በአሁኑ ሰዓት ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል የተረጋገጠ አንደኛው መንገድ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በአግባቡ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም ማህበረሰቡ በንቅናቄው ትክክለኛ የጭምብል (ማስክ) አጠቃቀምን በመማር እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን በትክክል በማድረግ እና ሌሎችም እንዲያደርጉ በማገዝ የቫይረሱን ስርጭት በመግታት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ዶክተር ሊያ በፌስ ቡክ ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.