Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለኖርዌይ እና ካናዳ አምባሳደሮች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከኖርዌይ እና ካናዳ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ።

አምባሳደሩ ለኖርዌዩ አምባሳደር ኑት ላንጌላንድ እና ለካናዳው አምባሳደር ክርስቶፈር ዊልኪ መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ ስላለው ህግን የማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

በዚህ ወቅትም ዘመቻው የንጹሃንን ደህንነት ታሳቢ ባዳረገ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።

አያይዘውም ህግ የማስከበር ዘመቻው የጥፋት ቡድኑን ለህግ በማቅረብ በቅርቡ ይጠናቀቃል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አምባሳደሩ ለቻድ እና ኒጀር እንዲሁም መቀመጫቸውን አልጄሪያ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትም በመንግስት እየተወሰደ ስላለው ህግ የማስከበር ዘመቻ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.