Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓለም አቀፍ ጉዳዮች እና ምክትል ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚስተር ዴቪድ ኩኣሪ ጋር መከሩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓለምአቀፍ ጉዳዮች እና ምክትል ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚስተር ዴቪድ ኩኣሪ ጋር ለንደን ተገናኝተው መክረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ለአውሮፓ ሃገራት ግልፅ በሚያደርጉበት ዓለምአቀፍ ተልዕኮ እንግሊዝ ገብተዋል።

በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ተስፋ ሰጪ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ በሚደረጉበት ዓመታት፤ በወንበዴው የህውሃት ቡድን ሴራ በህዝቡ እና በመንግሥት በርካታ ጥፋቶች እንደተፈፀሙ አስታውሰዋል።

በዚህ መሰረት መንግሥት ህግ የማስከበር እርምጃ ለመውሰድ መገደዱን እና ጥፋተኞችን ለህግ የማቅረብ ጠንካራ እንቅስቃሴ ውስጥ መገባቱን አስረድተዋል።

ሚስተር ዴቪድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም እና ፀጥታ ለቀጠናው መረጋጋት ከፍተኛ ትርጉም እንዳለው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እና ፀጥታ እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጓን ያስታወሱት አማካሪው፤ በቀጣይም ለቀጠናው በዘላቂነት መረጋጋት የሰላም ምንጭ ሆና መቀጠል ይኖርባታል ~ ብለዋል።

መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ንፁህና ዜጎች እንዳይጎዱ እና የሰብዓዊ ድጋፍ መስጫ መንገዶች ማመቻቸት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

መንግስት ህግ በማስከበር እርምጃ ንፁሃን ዜጐችን ከማንኛውም አደጋ የመጠበቅ እና የመከላከል ዓላማ አስቀምጦ በሃላፊነት ስሜት እንደሚያስፈፅም በመግለፅ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ መስጫ ኮሪደሮች የማመቻቸት ስራ እንደሚጠናከር አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የተጀመረው ህግ የማስከበር ኦፐሬሽን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ አቶ ደመቀ ማረጋገጣቸውን ከፅ/ቤታቸው ያገፕነው መረጃ ያሳያል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.