Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የወጣቶች የሰላም መድረክ አየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ ሀገር አቀፍ የወጣቶች የሰላም መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

“ወጣትነቴ ለኢትዮጵያዬ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የንቅናቄ መድረክ ላይም ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የወጣት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛል።

የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ህይወት ሀይሉ በመድረኩ ላይ፥ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከገባችበት ችግር እንድትወጣ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተለይም በህወሓት አጥፊ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ክህደት እና ጥፋት ወጣቶች ከማውገዝ ባለፈ በየአካባቢያቸው ህብረተረቡን በማስተባበር ከመከላከያ ጎን መቆም ይገባቸዋል ሲሉም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ወጣቶች መንግስት ለጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ እሰከ መጨረሻው ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸውም አንስተዋል፡፡

የሰላም እጦት በሀገሪቱ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ከታሪክ በመማር ለተሻለ ለውጥ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ዋና ፅሀፊ ወጣት ኤርሚያስ ማቴወስ በበኩሉ፥ ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ እና የሰላም ግንባታ በምታደርገው ጥረት በጥቂት ቡድኖች እኩይ ተግባር የዜጎች ሞት፣ መፈናቀል እና ስደት በስፋት መስተዋሉን አንስቷል።

በተጨማሪም ዋና ጸሃፊው በሰሜን እዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመውን አስነዋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ወጣቶች ማውገዛቸውን ገልጿል።

ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ጥፋት አድራሾችን ለህግ አሳልፎ በመስጠት ሁሉም ወጣት ሊሰራ ይገባልም ብሏል።

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.