Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ከነገ ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት ይሰጣል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የፖሊዮ የክትባት ዘመቻ እንደሚጀመር የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ÷ ፖሊዮ በአሮሞ ብሄረሰብ ዞን ዳዋ ጨፋ ወረዳ በመገኘቱ ክትባት በሁለት ዙር ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስረድተዋል ።
ክትባቱ በአሮሞ ብሄረሰብ፣ በደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ዞኖች እንዲሁም በደሴ ከተማ አስተዳደር በሁለት ዙር የሚሰጥ ነው ብለዋል።
ክትባቱ እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ህጻናት የሚሰጥ መሆኑንም ዶክተር መልካሙ ገልጸዋል።
የፖሊዮ ወይም የእጅና እግር መልፈስፈስ የልጅነት ልምሻ በሽታ በመሆኑ ማህበረሰቡ ለክትባት ዘመቻው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሽታው ህፃናትን ለህመም፣ ለሞትና ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት /የእጅና የእግር መልፈስፈስ/የሚዳርግ መሆኑንም ተናግረዋል።
በሁለቱም ዙር ዘመቻ 865 ሺህ 284 ህፃናት እንደሚከተቡም ነው የተናገሩት፡፡
በናትናኤል ጥጋቡ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.