Fana: At a Speed of Life!

በአዶላ ከተማ 72 ሺህ 400 አዲሱ ሀሰተኛ ብር ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 17 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በአዶላ ከተማ 72 ሺህ 400 አዲሱ ሀሰተኛ ብር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
በዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ምክትል ኮማንደር በቃሉ በለጠ ÷ ሀሰተኛ የብር ኖቶቹ የተያዙት በአዶላ ከተማ ከህዳር 7 እስከ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች ውስጥ ወርቅና ሞተር ሳይክል ለመግዛት ከሞከሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች እጅ ነው።
በአዶላ ከተማ ሞተር ሳይክል ለመግዛት ከሞከረ አንድ ተጠርጣሪ 201 ባለ 200 አዲሱ ሀሰተኛ የብር ኖት መያዙን ገልጸዋል።
በዚሁ ከተማ ወርቅ ለማግዛት የሞከረ ሌላ ሁለተኛ ተጠርጣሪም 301 ባለ 100 አዲሱ ሀሰተኛ የብር ኖት ይዞ መገኘቱን አብራርተዋል።
ሶስተኛ ተጠርጣሪም 20 ባለ 100ና ሁለት ባለ 50 አዲሱ ሀሰተኛ የብር ኖት ተይዞ መገኘቱን ተናግረዋል ።
በአጠቃላይ 524 ሀሰተኛ የአዲሱ የብር ኖቶች መያዛቸውን ገልጸዋል።
በሀሰተኛ የብር ኖት ወርቅ ለመግዛት የሞከረ ተጠርጣሪ ለጊዜው አምልጦ በመሰወሩ ክትትል እየተደረገበት መሆኑን የገለጹት ኮማንደር በቃሉ፤ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።
የዞኑ ህዝብ እየተስፋፋ የመጣውን ሀሰተኛ የብር ኖት ዝውውርና ሌሎች ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ሲያጋጥሙት ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.