Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች በተቀላጠፈ መልኩ ድጋፍ እንደሚያቀርብ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2013 (ኤፍቢሲ) መንግስት በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች በተቀላጠፈ መልኩ ድጋፍ እንደሚያቀርብ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
እንዲሁም የሰብዓዊ ድጋፍ ከሚሰጡ አካላት ጋር በመሆን መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ እንደሚሰራ ነው ፅህፈት ቤቱ የገለጸው፡፡
በትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ሁኔታ የሚያጣራው ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ጉዳዩን ያጣራ ሲሆን የሰብአዊ ድጋፉ በሰላም ሚኒስቴር እና በፌደራል ባለድርሻ አካላት ቅንጅት በኩል እንደሚደርስ ነው የተጠቀሰው፡
በዚህም በፌደራል መንግሥት ቁጥጥር ሥር ባሉ አካባቢዎች የመጀመሪያ ድጋፍ የምግብ ፣ የመድኃኒት፣ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ስርጭት ከቀያቸው ውጭ በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ማቅረብ እንደተጀመረ ነው የተገለጸው፡፡
ኮሚቴው ባቀረበው ግምገማ መሰረት የዕለት ድጋፍ የሚሹ ዜጎች የተለዩ ሲሆን ሁኔታው እስከሚረጋጋ ድረስ ድጋፍ ያደርጋልም ነው ያለው ፅህፈት ቤቱ፡፡
መንግስት የተሰደዱ ዜጎች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ፣ ንጹሃን ዜጎችን ለመጠበቅና ለመደገፍ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሰብዓዊ ድጋፍ ከሚያደርጉ ድርጅቶች ጋር ይሰራልም ነው የተባለው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.