የሀገር ውስጥ ዜና

56 ኢትዮጵያውያን ከቤሩት ተመለሱ

By Abrham Fekede

November 26, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 56 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከቤሩት ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡

ዛሬ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት በዘጠነኛው ዙር ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ተመዝግበው ከነበሩ ሰነድ አልባ ዜጎች መካከል መሆናቸውን ከቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡