Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከ55 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ ባለ 200 የብር ኖት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በአዲስ አበባ በልደታ ክፍለ ከተማ ከ55ሺ ብር በላይ ሀሠተኛ ባለ200 የብር ኖቶች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ከተያዘው የብር ኖት ባለፈ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል።
ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ተግባረድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሠብ አዲሱን ባለ200 የብር ኖቶ በመቶ ብር ለመቀየር በማፈላለግ እያለ ከህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሠው ጥቆማ መሠረት ግለሰቡ ከ7 ሺህ 400 ሀሠተኛ ባለ2መቶ የብር ኖት ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።
በፖሊስ ከተያዘው አንድ ተጠርጣሪ መረጃ በመነሳት በተደረገው የክትትልና የኦፕሬሽን ስራ ከተያዘው ተጠርጣሪ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሶስት ተጠርጣሪዎች እና 48ሺህ 200 ሀሠተኛ ባለ2መቶ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ዋና ሳጅን በእምነት ግርማ ተናግረዋል።
ከአዲሱ የብር ኖት ቅያሬ ጋር ተያይዞ በርካታ አዲስ ሀሠተኛ የብር ኖቶች ተመሳስለው እየተሰሩ ወደ ህብረተሠሰቡ እየተሠራጩ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጥበት እንደሚገባ ዋና ሳጅን በእምነት ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ ግብይት በሚያከናውኑበት ወቅት በአጭበርባሪ ግለሰቦች እንዳይታለልና እንዳይጭበረበር ጥንቃቄ ማድረግና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.