Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 560 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 427 ሰዎች ደግሞ ከቫይረስ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 789 የላቦራቶሪ ምርመራ 560 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 107 ሺህ 669 ደርሷል።
በትናንትናው ዕለት 427 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በዚህም በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 67ሺህ 1 መድረሱ ነው የተነገረው።
ከዚህ ባለፈም የ8 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 672 መድረሱንም ሪፖርቱ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.