Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዦ ኢቭ ለድሪዮ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዦ ኢቭ ለድሪዮ ጋር ተወያዩ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

በትግራይ ክልል የተጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን በተመለከተም በዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መንግሥት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ የጀመረውን ህግ የማስከበር እርምጃ በጥንቃቄ ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚመራ አስታውቀዋል።

በዘመቻው ንፁሃን ዜጐችን ከከፋ አደጋ የመጠበቅ እና የመከላከል ዓላማ አስቀምጦ በሃላፊነት እንደሚያከናውንም አስረድተዋል።

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ አካላት በቀጠናው የሚንቀሳቀሱበት ነፃ ኮሪደር ክፍት የማድረግ ስራ በመንግሥት በኩል መመቻቸቱንም ጠቅሰዋል።

አሁን ላይ መከላከያ ሰራዊት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ወንጀለኞች ለህግ በሚቀርቡበት አጀንዳ ዙሪያ ውይይት ተጀምሯልም ነው ያሉት።

የተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መናገራቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.