Fana: At a Speed of Life!

ህግን የማስከበር እምርጃው የትግራይን ህዝብ ከህወሓት ጁንታ የመከላከል ዓላማ ያለው ነው – አቶ አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ የሚገኘው ህግን የማስከበር እምርጃ የትግራይን ህዝብ ከህወሓት ጁንታ የመከላከል ዓላማ ያለው መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገለፁ።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ የሚገኘውን ህግን የማስከበር እርምጃ አስመልክቶ ከፍራንስ 24 ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የህወሓት ጁንታ የዘር ማጥፋት ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል እና የግዛት አንድነቷን የማስጠበቅ መብት አላት ብለዋል።

በትግራይ ክልል እየተወሰደ የሚገኘው እርምጃ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሚደረግ ህጋዊ ዘመቻ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ።

ዘመቻው የሀገር ውስጥ ጉዳይ እንደሆነ ያነሱት አቶ አህመድ የሀገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የደህንነት ተቋማት ዘመቻውን ለመፈፀም በቂ አቅም አላቸውም ነው ያሉት።

ሚኒስትሩ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን በተመለከተ መንግስት ከሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ ዘመቻ መቐለ ከተማን ጨምሮ በመላው የትግራይ ክልል ህግና ስርዓትን ለማስጠበቅ እና ወንጀሎችን ለህግ ለማቅረብ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ሚኒስትሩ በቆይታቸው ህግን በማስከበር እርምጃው በህወሓት ቁጥጥር ስራ የነበሩ በርካታ አካባቢዎችን የሃገር መከላከያ እንደተቆጣጠራቸውም አስረድተዋል፡፡

እየተካሄደ የሚገኘው ህግን የማስከበር እርምጃ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.