የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ህዳር 24 እና 25 ቀን ይሰጣል 

By Abrham Fekede

November 27, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ህዳር 24 እና 25 ቀን እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ፈተናው በሁለት ቀናት ይሰጣል፡፡

ትምህርት ቢሮው ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች ሰዓቱን ጠብቀው እንዲገኙ አሳስቧል፡፡