Fana: At a Speed of Life!

ሁለት የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃዶችን ለመስጠት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ መጠየቂያ ሰነድ ወጣ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ሁለት ብሄራዊ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃዶችን ለመስጠት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ መጠየቂያ ሰነድ ማውጣቱን ይፋ አደረገ።

የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ በሰጡት መግለጫ ውድድሩ ፍትሃዊ እንዲሆን የሚያስችለው ሂደት ተገባዶ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃዶችን ለመስጠት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ መጠየቂያ ሰነድ ማውጣቱን ገልፀዋል።

ጨረታው ለሶስት ወራት እንደሚቆይ የገለፁት ዶክተር እዮብ ከዚህ ቀደም ፍላጎት ያሳዩትን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሳተፉ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

በዚህም ፍቃዱ እስከ ሚያዝያ ወር 2013 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል ብለዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ባልቻ ሬባ በበኩላቸው የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃዶችን ለመስጠት የሚሰራው ስራ በጥንቃቄ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሰነዱም በባለስልጣኑ ድረገጽ እንደሚገኝ እና በቅርቡም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ህትመት እንደሚኖረውም አስረድተዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.