Fana: At a Speed of Life!

ቋሚ ኮሚቴው ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በመከላከልና መቆጣጠር ረገድ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ የመስክ ምልከታ አድርጓል ፡፡
በምልከታው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከጅቡቲ ተመልሰው በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ ከነበሩ 1 ሺህ 423 ተመላሾች መካከል ለ125 ሴት ተመላሾች የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን በሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኦሞግ ገልፀዋል፡፡
ተመላሾቹ የቆይታ ጊዜያቸውን ጨርሰው አስፈላጊው ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ከሚያዝያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መኖሪያቸው የመመለሱ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ወይዘሮ አለሚቱ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ አያይዘውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለዘጠኝ ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተለያዩ መገናኛ ስልቶችን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠቱን መናገራቸውን ከህዝብ ተወካች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እቅዶችን አውጥቶ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከመከላከል አኳያ እየሰራ ያለውን ስራ በጥንካሬ ያነሳ ሲሆን ÷የተፈጠሩት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቀጣይም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝቧል ፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.