Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አፋን ኦሮሞና ሶማልኛን በሁለቱ ክልሎች ማስተማር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አፋን ኦሮሞና ሶማልኛን በሁለቱ ክልሎች ማስተማር በሚቻልባቸው ዝግጅቶች ላይ ተወያዩ፡፡

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶና የሶማሌ ክልል አቻቸው አቶ መሀመድ ፈታህ መሀመድ በዝግጅቶቹ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ዶክተር ቶላ የሁለቱ ክልል ህዝቦች በርካታ የጋራ እሴቶች እንዳላቸው ገልፀው ቋንቋዎቹን ማስተማር የበለጠ ትስስር እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

የኦሮሞና የሶማሌ ህዝብ አንድነቱ ይበልጥ እንዲጠናከር ቋንቋዎቹን በሁለቱ ክልሎች በትምህርት መስጠት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሶማሌ ክልል የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ በበኩላቸው ቋንቋዎቹን ማስተማር በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትስስሮሽ እንደሚያጠናክር ተናግረዋል፡፡

የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከርና ሁለንተናዊ ትውውቅን ለማዳበር ይረዳልም ነው ያሉት፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በተመረጡ ወረዳዎች ላይ ለሙከራ ሊጀመር የታቀደው ቋንቋውን የማስተማር ስራ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

የህዝቦችን የጋራ እሴቶች ማዳበር ትውልድ ይበልጥ አንድነቱ እንዲጎለብት ይረዳልም ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.