Fana: At a Speed of Life!

በመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት መፈፀም በየትኛውም ሀገር ተቀባይነት የሌለው ነው- ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የህወሃት ቡድን በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለተከሰቱ ጥፋቶች እና ከፍተኛ ወንጀሎች ተጠያቂ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ገለጹ።

ቡድኑ በሀገር ጦር ሰራዊት ካምፕ ላይ የፈፀመው ወንጀል ሉዓላዊነት መዳፈርና በየትኛውም ሀገር ቢሆን ተቀባይነት የሌለው ድርጊት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
መንግሥትም በዚህ ምክንያት ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ ገብቷል ነው ያሉት፡፡

ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከቢቢሲ ሃርድ ቶክ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ የህወሃት ቡድን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለተከሰቱ ጥፋቶች እና ከፍተኛ ወንጀሎች ተጠያቂ መሆኑን አስረድተዋል።

መንግስትም በቡድኑ የከፋ ጥፋት ምክንያት ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ መግባቱን ነው ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ያስታወቁት።

የህግ ማስከበር ዘመቻው የተጀመረው የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አበላት ላይ ባደረሰው ጥቃት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጦር ሰራዊት ካምፕ ላይ የሚደረግ ጥቃት ደግሞ በየትኛዋውም ሉዓላዊ ሀገር ቀይ መስመር የማለፍ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

የፌዴራል መንግስት በየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎች ህግን የማስከበርና የሀገር ህልውናን የማስጠበቅ ስልጣንና ሃላፊነት ያለበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መንግስት ህግ በማስከበር ዘመቻው ንጹሀን ዜጎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ እያደረገ ነውም ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.